Saved to Favorites!

የቦታ ስፋት 76.5ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,282,199.50 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ 50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡

Source | ምንጭ

አዲስ ዘመን ሰኔ 27/2018

Closing | መጨረሻ

Jul 08, 2026

Views | እይታዎች

55

Region | ክልል

Addis Ababa

Doc Price

_ ETB

CPO / Conditions | ሁኔታዎች

1/4

Description | ዝርዝር መግለጫ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትዕግስት እሸቱ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ብርቄ ካሳዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/246181 በ2/6/2017 १/१० ५१ ०५/०//145715 025/3/2017/145715 030/06/2018  በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ የካርታ ቁጥር ወ2/ወዝ01/394/10801/00 በሴሪ ቁጥር 001289 የሆነው ይዞታ የክፍሉ መሬት አስተዳደር በ30/06/2018 ዓ.ም ባደረገው ክፍፍል በ"A" የተመለከተው የቦታ ስፋት 76.5ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,282,199.50 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ 50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

PDF Export is locked for your plan.